የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረታዊ ዓላማዎች፣ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዋና ዘርፎች ግቦችን፣ የአቅም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ተግባሮችን እውን ለማድረግ የሬዴራል አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 691/2003 የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሚል ስያሜ በጋራ ሲሰሩ የነበሩ የሥራ ዘረፎች በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በተናጠል እንዲደራጁ ተደርጎ በአዋጅ ቁጥር 916/2007 የንግድ ሚኒስቴር ተቋቁሟል፡፡

ተልዕኮ

አሰራርን ግልፅ፣ ተደራሽና ውድድር የሰፈነበት እንዲሆን በማድረግ፣ ፍትሃዊ ንግድ በማስፈንና  ለሀገር በቀል ባለሃብቱ የላቀ አገልግሎትና ድጋፍ በመስጠት እና የዘርፉን የሰው ሀብትና የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ፣ ውጤታማ የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት የአምራቹን፣ የሸማቹንና የንግዱን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡

Goals

Duties and Responsibilities

 1. የአገር ውስጥ ንግድ እንዲስፋፋና ህጋዎ አሰራር እንዲሰፍን ተገቢነት ያላቸውን እርምጃዎች ይወስዳል፤
 2. የአገሪቱ የወጪ ንግድ የሚስፋፋበትና የሚጠናከርበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ ላኪዎች ድጋፍ ይሰጣል፤
 3. የወጪና ገቢ እቃዎች በትክክለኛ ዋጋ ስለመሸጣቸው ወይም ስለመገዛታቸው ለማረጋገጥ የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል ፤ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ክትትል ያደርጋል፤ ዋጋ አሳንሰው የሚልኩ እንዲሁም አሳንሰው ወይም አስበልጠው በሚያስመጡ ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ይወስዳል፤
 4. የውጭ ንግድ ግንኙነቶችን ይመሰርታል፤ ድርድሮችን ያስተባብራል፤ የንግድ ስምምነቶችን በህግ መሰረት ይፈራረማል፤ ያስፈጽማል፤
 5. ፀረ ውድድር ተግባራትን ለመከላከል የሚየስችል የተሟላ ስርዓት ይዘረጋል፤ አፈፃጸሙን ይከታተላል፤ በህግ አግባብ ለሸማቾች ጥበቃ ያደርጋል፤
 6. አግባብ ባላቸው ህጎች መሰረት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን ይሰጣል የተሰጡ የንግድ ስራ ፈቃዶች ለተሰጠባቸው ዓላማዎች መዋላቸው ይቆጣጠራል፤
 7. የአክስዮን ማህበራት የባለአክሲዮኖችንና ህብረተሰቡን ጥቅም በሚያስከብር ደረጃ እንዲቋቋሙና እንዲሰሩ ድጋፍ ይሰጣል፤ ክትትል ያደርጋል፤
 8. የዋጋ ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ መሰረታዊ የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን ዋጋ እያጠና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀርባል፤ሲፈቀድም ተግባራዊነታቸው ይከታተላል
 9. የሀገሪቱን ህጋዊ ስነ-ልክ ስርዓት ይዘረጋል መተግበሩን ይቆጣጠራል አስፈፃሚ አካላትን ያስተባብራል፤
 10. የወጪና ገቢ ንግድ እቃዎችን ጥራት ይቆጣጠራል ተፈላጊውን የደረጃ መስፈርት የማያሟሉ የንግድ እቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ወይም ከሀገር እንዳይወጡ ያግዳል ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
 11. አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸው የንግድ እቃዎችና አገልግሎቶች የደረጃውን መስፍርት ማሟላታቸውን ይቆጣጠራል ከተዘጋጀላቸው ደረጃ በታች ሆነው በተገኙበት ላይ እርምጃ ይወስዳል፤
 12. በሌሎች አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የሚሰራባቸው አስገዳጅ ደረጃዎች በተቀናጀ መልኩ እንዲተገብሩ ያደርጋል፤ በአፈጻጸም ላይ የሚወያይ ጉባኤ ይጠራል መድረኩንም ይመራል
 13. የአገሪቱን የንግድ መደረጃዎች ያደርጃል ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል
 14. የሸማቾችን ጨምሮ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶችን እንዲቋቋሙ ያበረታታል የተ ቋቋሙትንም እንዲጠናከሩ ያደርጋል፤

ራዕይ

በ2022 በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የንግድና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሆን፤