የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት

ኢተምድ የሚለው ምህፃረ ቃል ፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት” ይወክላል፡፡ ኢተምድ በጥር ወር 2003ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 196/2003 በፌደራል ደረጃ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተቋቁሟል፡፡ የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡ ኢተምድ በዋነኝነት የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች ማለትም የላብራቶር ፍተሻ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በስሩ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ይዞ 8ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመላው ሀገሪቱ በማደራጀት እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

አድራሻ ገርጂ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የአገሪቱን ግብርና በገበያ ላይ ወደተመሰረተ የአመራረት ስርዓት ለማሸጋገር እንዲሁም አነስተኛ የግብርና አምራቾች በገበያው ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ፍትሃዊ ለማድረግ በማሰብ ቀልጣፋ፣ ስርአት ያለውና ወጥነት ያለው የግብርና ምርቶች የሚገበያዩበት  የገበያ ስርዓት ለመፍጠር በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 550/2007 መሰረት በ2000 ዓ.ም የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

አድራሻ ሜክሲኮ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት

የራሱ ሕጋዊ ስብዕና ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ ተቋቋመ። ተልእኮ እንደ ሶስተኛ ወገን ዕውቅና ፣ የተስማሚነት ግምገማ አካላት (ሲኤቢኤስ) እንደ ሙከራ ፣ መመዘኛዎች ፣ የምስክር ወረቀቶች ወይም ምርመራዎች ያሉ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ማከናወን ዕውቅና መስጠት ነው።

አድራሻ ቦሌ ክፍለከተማ መገናኛ ከአምቼ አጠገብ

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

በአገራችን የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ተቋም በመንግሥት ሲጠናና ሲቋቋም መነሻ መሠረቱ የካቲት 1973 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መንግሥትና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም መካከል የተደረገው የእርዳታ ስምምነት ነበር፡፡ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ንዑስ ዘርፍ ኢንዱስትሪዎች ችግር ውስጥ በነበሩበት ወቅት የኢንጂነሪንግ ዲዛይንና ቱል ድርጅት 1975 ዓ.ም. ተፀነሰ፡፡በ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ተደርጎ የሽግግር መንግሥቱ አዲስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መተግበር መጀምሩ የድርጅቱን መፈጠር እንዲጎላ አድርጓል፡፡የኢንጂነሪንግ ዲዛይንና ቱል ድርጅት ሲመሰረት ዓላማው መሳሪያዎች፣ቱሎችና ሌሎች ቁሳዊ ግኝቶችን ዲዛይን አድርጎ በመፈብረክ ለብሔራዊ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ማድረግ ነበር፡፡

አድራሻ ገርጂ አካባቢ