ነዳጅ

የነዳጅ የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ

 በሚያዚያ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ የግንቦት ወር የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል ተወሰነ

በሚያዚያ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ የግንቦት ወር የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል ተወሰነ

===================================

አዲስ አበባ 28/08/2013 ዓ.ም (ንኢሚ) ከአውሮፕላን የነዳጅ ምርቶች ውጭ ያሉ ሌሎች የነዳጅ ምርቶች በሚያዚያ ወር ሲሸጡበት በነበረው ዋጋ የግንቦት ወር የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል የተወሰነ ሲሆን የአውሮፕላን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ተሰልቶ የተገኘው 11 ሣንቲም በመጨመር በሚያዚያ ወር ሲሸጥበት ከነበረው 43.70 ወደ ብር 43.81 ከፍ እንዲል ተወስኗል፡፡