22የኢኮኖሚ ስብራት በእግሩ መልሶ እንዲቆም ያስቻለ ማርሽ ቀያሪ የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ መጀመራችንም ውጤት አሳይቷል ተባለ፡፡
አዲስ አበባ 03/12/2013 ዓ.ም (ንኢሚ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ሀገራዊ የወጪ ንግድ የዕውቅና መድረክ ተገኝተው እንደተናገሩት ባለፈው ዓመት ዓለም ዓቀፉን የኮሮና ወረርሽኝ ጫና ተቋቁመን ከሶስት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ እንዲሁም በ2013 በጀት ዓመት 3.64 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማስመዝገባችን በቅንጅት ከተሠራና አመራር ከተሰጠ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አመላካች ነው፡፡ መንግስት በዘርፉ በተወሰደው ብልህ ውሳኔ ከዓመታት ተከታታይ ማሽቆልቆል ተሻግሮ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተመዘገበውን ከፍተኛ የወጪ ንግድ የአፈፃፀም እድገት እውን ማድረግ መቻሉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ጠቁመዋል፡፡