በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ አሰራሮችን በማክሰም በሀገራችን ላይ የተከፈተውን የኢኮኖሚ ጦርነት መቀልበስ ያስፈልጋል

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር  አመራሮች ከፌደራል የዋጋ ንረት፣ ህገ-ወጥና ኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይል ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደተገለፀው ሀገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመጠቀም የንግድ ስርዓቱን  በማዛባት በሀገርና ህዝብ ላይ የኢኮኖሚ ቀውስ በመፍጠር ዘርፉን ሌላ የጦርነት ሜዳ ለማድረግ እየሰሩ የሚገኙ ህገ-ወጦች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ  በሀገራችን ላይ የተከፈተውን የኢኮኖሚ ጦርነት በመቀልበስ የሸማቹንና የሻጩን የግብይት ሚዛናዊነት ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው፡፡
የግብረ ሀይሉ አባል ተቋማት ወቅታዊ የዋጋ ማረጋጋት፣ ሕገ-ወጥ እና ኮንትሮባንድ ንግድን ከመቆጣጠር አኳያ እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትን የተገመገመ ሲሆን ከወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በቅንጅት መስራት አለብን ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገ/መስቀል ጫላ ተናግረዋል፡፡
ከዋጋ ንረቱ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ህገ-ወጥ ሥራዎች ለመቆጣጠር የአጭር ጊዜና በረጅም ጊዜ ዕቅድ በማዘጋጀት መፍትሔ እየተሰጠባቸው ስራዎችን ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በቀጣይ የሀገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በየደረጃው ያሉ አካላትን እና ተቋማት ተግባርና ሀላፊነት ላይ መግባባት በመፍጠር አጀንዳ አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በምግብና ምግብ ነክ ምርቶች ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት በመቅረፍ ሕብረተሰቡን ከኑሮ ውድነት መታደግ እና ሕገ-ወጥና ኮንትሮባንድ ንግድን በመከላከል ሀገሪቱ ከወጪ ንግድ የምታገኘውን ገቢ ማሳደግ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አቶ ገ/መስቀል አሳስበዋል፡፡

Share this Post