የፀረ-ሙስናን ቀን ተከበረ

አዲስ አበባ፣ 30/03/2014ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ በሃገራችን ለ17ኛ ጊዜ "በስነምግባር የታነጸ አመራር ከሙስና ለጸዳች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለው የፀረ-ሙስና ቀን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ አክብረዋል፡፡
በበዓሉ አከባበር ላይ የስነ ምግባርና ፀረ- ሙስና መከታተያ ዳይሬክተር ኤልሳቤጥ በየነ እንደገለጹት በሃገራችን እየተስተዋለ ለሚገኘው ሙስና መሠረታዊ ጉዳዩ በመንግስት መ/ቤቶች ያለው ብልሹ አሰራር በመሆኑ ሃገራችን ከሙስና የጸዳች እንድትሆን ይህንን ብልሹ አሰራር በጋራ መዋጋትና ማስወገድ ይገባል፡፡ ይህንን ለማድረግም ከአመራሮች ጥረት በተጓዳኝ የሁሉም ዜጋ ቁርጠኝነት ሚና የላቀ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሯ ሙስናን ለመዋጋት ዋንኛው ስልት መረጃ በመሆኑ ግለሰቦች ጥቆማ ሲሰጡ በቂ መረጃ መያዝ ይገባቸዋልም ብለዋል፡፡

Share this Post