በወጪ ንግድ ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥር እየተደረገ ነው

ወደ ውጪ ሀገራት የሚላኩ የግብርና ምርቶች ከኢትዮጲያ ደረጃ መስፈርት በተጨማሪ በተቀባይ ሀገራት መስፈርት መሰረት ላኪዎች የሽያጭ ኮንትራት ስምምነት መስፈርትን አሟልተው እንዲልኩ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ሦስት ወራት በ130,000 ሜትሪክ ቶን የወጪ ምርቶች ላይ የኢንስፔክሸን ሥራ ለማከናወን አቅዶ በቁጥር በ111,693.8 ሜትሪክ ቶን ወጪ  ምርቶች  ላይ የኢንስፔክሽን ስራ በመስራት ፈቃድ ሰጥቷል ፡፡
በተደረገው የጥራት የቁጥጥር ስራ 166ሜ.ቶን አኩሪ አተር እና 120ሜ.ቶን ዥንጉርጉር ቦለቄ በላቦራቶሪ ፍተሻ በኢምፒውሪቲ ፓራሜትር የጥራት መስፈርትን ባለማሟላቱ ከእንደገና እንዲበጠር በማድረግ ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲላኩ  በማድረግ የሀገራችንን የወጪ ምርት ተፈላጊነት የማሻሻል ስራ ተሰርቷል፡፡

Share this Post