ሌብነትን በመጠየፍ ከሌብነት የተላቀቀ ከራሱ ይልቅ ቅድሚያ ለሀገሩ ዕድገት የሚተጋ አመራርና ባለሙያ መፍጠር ያስፈልጋል

አዲስ አበባ 29/02/2014 ዓ.ም (ንቀትሚ) ለክልልና ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ኃላፊዎች ስለ አዲሱ ንግድ ህግ፣ የበየነ መረብ ንግድ መዝገባና ፈቃድ እና  ስለ ነዳጅ አቅርቦትና ቁጥጥር ስርዓት ገለፃ በተደረገበት ወቅት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ ገ/መስቀል ጫላ እንደገለፁት አመራሩ ከላይ እስከታች ሌብነትን የተጠየፈ ከሆነ በሌብነት የንግድ ስርዓቱን በማዛባት የሀገርንና የህዝብን ኦኮኖሚ የሚበዘብዙ ባለሙያዎችና ተገልጋዮች ላይ የማያዳግም እርምጃ  በመውሰድ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትና ለህዝብ የኑሮ ደህንነት የሚጨነቅ፤ ከራሱ በላይ  ለሀገሩና  ለህዝቡ ዕድገት ቅድሚያ በመስጠት የሚተጋ አገልጋይ ባለሙያና የዘርፉ ተገልጋይ  በመፍጠር   ዘርፉን ፍትሀዊ፣ ቀልጣፋና በውድድር ላይ የተመሰረት ማድረግ ቀላል ይሆናል ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅት ፈታኝና እንቅልፍ የሚነሳ በመሆኑ ግንባር ላይ ከሚደረገው የጦርነት ትግል ባልተናነሰ የንግድ ስርዓቱን በማዛባት የኢኮኖሚ ጦርነት ከፍተው ወደማንወጣው ማዕበል ውስጥ ሊከቱን የሚሹ ሆድ አደር የዘርፉ ተላላኪዎችን የንግድ ስርኣቱን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመምራት አደብ ማስገዛትና የሀገራችንን ኢኮኖሚና የህዝባችንን የኑሮ ሸክም ልናቀልና ልናሻሽል ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ ወቅቱ ሰብሎች የደረሱበት ጊዜ በመሆኑ አመራሩና ባለሙያው ከላይ እሰከታች በመቀናጀት፣ በመደጋፍና በመናበብ አርሶ አደሩን በመደገፍ ሰብሉ በወቅቱ ተሰብስቦ ለገበያ እንዲቀርብ ሌት ከቀን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

Share this Post