የስንዴ ፍላጎትን ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ 07/03/2014 (ንቀትሚ) የዳቦ ስንዴ ፍላጎትን ለማሟላት በሀገር ውስጥ ምርት የማይሸፈነውን በግዥ ለማቅረብ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የዳቦ ስንደ አቅርቦትን ለማሻሻል የተለያዩ የግዥ ሂደቶች እየተከናወኑ ሲሆን 1ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በግዥ ሂደት ላይ መሆኑን የንግድ ዕቃዎች ዋጋ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ አሸናፊ ማሙየ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውስጠም የ300 ሺህ ሜትሪክ ቶን ጥሬ ስንዴ የግዥ ጨረታ ህዳር 8/2014፣ የ400 ሽህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ጨረታ  ደግሞ ህዳር21/2014 እንደሚከፈት የገለጹት አቶ አሸናፊ በመንግስት ልዩ የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ በተወሰነው መሰረት 300ሽ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በUN agency ግዥ በሂደት ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
 ምርቱን ከውጪ ገዝቶ ለማቅረብ የአለም አቀፍ ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር እንተግዳሮት መሆኑን የጠቀሱት ቡድን መሪው ይህንን በግዥ ሂደት ላይ ያለውን ሥንዴ በቅንጅት ክትትል በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ ጊዜውን ጠብቆ እንዲገባና ለገበያ ማረጋጊያ እንድውል ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል፡፡

Share this Post