የአፍሪካ ጨርቃጨርቅና ቆዳ አልባሳት የፋሽን ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣25/03/2014 ዓ.ም (ኢሚ) የአፍሪካ ጨርቃጨርቅና ቆዳ አልባሳት የፋሽን ዐውደ ርዕይ ህዳር 24/2014 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተከፍቷል፡፡
ዐውደ ርዕይው  እስከ ህዳር 26/2014 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በመርሀ ግብሩም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትና የዘርፉ ሀገር በቀል አምራቾች ተሳትፈውበታል፡፡ የዐውደ ርዕዩ ዋና ዓላማ በአህጉር አቀፍ ደረጃ የምርት ትውውቅና የገበያ ትስስር ከመፍጠር በተጨማሪ በተለይ አሁን ላይ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ፀረ- ኢትዮጵያ ሀገራትና ሚዲያዎች እንደሚያናፍሱት  አሉባልታ ሳይሆን የተረጋጋችና ሰላም የሰፈነባት ከተማ መሆኗን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማረጋገጫ ሁነት እንደሆነ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒትር ዴኤታ አቶ ሽሰማ ገብረስላሴ በመርሀግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግራቸው አስረድተዋል፡፡

Share this Post