የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአለም የነዳጅ ዋጋን ባገናዘበ መልኩ ከዚህ ወር ጀምሮ የነደጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ አደረገ፡፡
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የንግድ አሰራርና ላይሳንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሐሰን መሀመድ እንገለጹት መንግስት ላለፉት ስምንት ወራት የህዝቡን የኑሮ ውድነት በመገንዘብ የነዳጅ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ሳይደረግ መቆየቱንና አሁን የአለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መፍጠሩን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጿል፡፡
የነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ እስከ ህዳር/2014 ዓ.ም ድረስ
82, 204, 842 ,776 ብር ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት በመሆኑ ይህ ሁኔታ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሀገሪቱ የነዳጅ ፍጆታዋን ከመግዛት አንጻር አሉታዊ ተዕጽኖ የሚያሣድር በመሆኑ የዋጋ ማስተካከያው አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ የአለም አቀፍ ዋጋን ተሳቢ በማድረግ ተሰልቶ ከመጣው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ 25 በመቶ ህዝብ እንዲከፍል በማድረግ 75 በመቶን በመንግስት የሚሸፈን በማድረግ በዚህም 6ቢሊዮን ብር ኪሳራ በመንግት ላይ እንደሚደርስ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስጣን አቶ አህመድ ቱሳ ተገልጿል ፡፡
ከዘሬ ጀምሮ ቤንዚን{MGR} ብር 31.74፣ ነጭ ጋዝ{Kerosene} ብር 28.93፣ ነጭ ናፍጣ {ADO} ብር 28.93፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ {Light Fuel Oil} ብር 23.73፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ {Heavy Fuel Oil} ብር 23.29 እና የአውሮፕላን ነዳጅ {Jet fuel} ብር 58.77 ብር በሊት እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡

Share this Post