አንዳንድ ኩባንያዎችና የነዳጅ ማደያዎች ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር እያደረጉ ካለው ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አዲስ አበባ 25/05/2014 ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከጥር 26/2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2014 ዓ.ም ድረስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲሸጥ ወስኗል፡፡

መንግስት ነባራዊ የዓለም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በመጨመር ላይ ቢሆንም ውሳኔው የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል መሆኑን እየገለፅን በዘርፉ በየተሰማራችሁ ተዋንያን ከህገወጥ እንቅስቃሴዎች እንድትቆጠቡ እያሳሰብን የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት ያልተገባና ህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኩባንያዎችና ማደያዎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Share this Post