የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተሻሻለውን የንግድ ህግና ፓሊሲዎች በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ 30/05/2014(ንቀትሚ) በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተሻሻለውን የንግድ ህግ፤ የአለም ንግድ ድርጅት የአባላነት ሂደት፤ የውጪ ፖሊሲ እና ብሔራዊ የጥራት ፖሊሲ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገ/መስቀል ጫላ የግንዛቤ ማስጨመጫ ስልጠናዊ ለቋሚ ኮሚቴው መሰጠቱ በተሻለ መልኩ ሚኒስቴር መ/ቤቱን ለመደገፍና የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት የሚኖረው ሚና የላቀ ነው  ያሉ ሲሆን እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች  ወደፊትም እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

Share this Post