ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 29ኛውን የአካል ጉዳተኞች ቀን በቸሻየር ኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል አከበረ

አዲስ አበባ፣30/03/2014 ዓ.ም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዓለም ለ30ኛ በሀገራችን ለ29ኛ ጊዜ “የአካል ጉዳተኞችን መሪነትና ተሳትፎን በማረጋገጥ አካታች፣ተደራሽና ዘላቂ ድህረ ኮቪድ-19 አለም እንገንባ!!” በሚል መሪ ቃል እተከበረ ያለውን የአካል ጉዳተኞች ቀን በቲሻየር የአካል ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል ተገኝቶ አክርብሯል፡፡

ቸሻየር የአካል ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል በ1962 እ.ኤ.አ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ህፃናት ማገገሚያነት የተመሰረተ ሲሆኑ በአሁኑ ሠዓት በተለያየ ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ማንኛውም ሰው የአገልግቱ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከድር ቃሲም ገልጸዋል፡፡

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ዳምጤ እንደገለፁት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የብረታ ብረት፣የቆዳና የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶችን ለማዕከሉ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

Share this Post