ከኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙዩኒኬሽን ዕቃዎች 3.7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ 01/03/2014(ንቀትሚ) በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙኒኬሽን ዕቃዎች 3.7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡
በሩብ ዓመቱ ከተለያዩ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙኒኬሽን ዕቃዎች ወጪ ንግድ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 3.7 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፀሀየ ይነሱ ገልፀዋል፡፡
የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን የግብይት አቅም ለማሳደግ የምርትና የግብዓት ትስስር የመፍጠርና ቅንጅታዊ አሰራርን የማጎልበት ስራዎች መሰራታቸውን የጠቀሱት አቶ ፀሀዬ ኢንቨስትምንትን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች 4 ፕሮጀክቶች ወደ ማምረት የተሸጋገሩ ሲሆን 3 ኢንተር ፕራይዞች የማስፋፊያ ስራ ማከናወናቸውን አክለው ገልፀዋል፡፡

Share this Post