ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ከ658 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

አዲስ አበባ፣9/6/2014 (ንቀትሚ)  ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት 145 ሺህ 321 ነጥብ 73 ቶን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 461 ነጥብ 81 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ 169 ሺህ 748 ነጥብ 30 ቶን በመላክ 658 ነጥብ አንድ ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አግኝታለች።

አፈጻጸሙ በባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ጋር ሲነጻጸር በመጠን የ52 ነጥብ 43 በመቶ፤ በገቢ ደግሞ የ302 ነጥብ 51 ሚሊዬን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

የቡና ኤክስፖርት በተናጠል ሲታይ በበጀት አመቱ ሰባት ወራት 162 ሺህ 818 ነጥብ 04 ቶን ቡና በመላክ 645 ነጥብ 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቷል፡፡ ይህም ከእቅዱ አንጻር በመጠን 119 በመቶ እንዲሁም በገቢ 143 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

Share this Post